“ ለእንቁጣጣሽ የሙዚቃ ዝግጅት ላማሳየት ውጭ ህገር ሄጄ ድምጼ ተዘግቶ ሳልዘፍን የቀረሁበት አጋጣሚ የማልረሳው አሳዛኝ ገጠመኜ ነው፡፡ ” ድምጻዊት ብጽአት ስዩም

.

Artist Bitsat Seyum Source: Bitsat Seyum

ድምጻዊት ብጽአት ስዩም አውስትራሊያን አገሬ ብላ ኑሮዋን ከጀመረች 13 አመታትን አስቆጥራለች ፡፡ በህይወት ዘመኔ ብዙ አገሮችን ለማየት ችያለሁ ይሁንና አውስትራሊያን የሚያክልብኝ ማንም አገር የለም ትላላች ፡፡ ድምጻዊት ብጽአት የአንቁጣጣሽ የሙዚቃ ዝግጅቷን ለማሳየት በመጣችበት ጊዜ ነበር አውስትራሊያን ለመጀመሪያ ያየቻት ፡፡ ካለችበት ከሜልበርን ከተማ የእንቁጣጣሽ እንግዳ አድርገናት ስለሙዚቃ ሰራዎቿ የቤተሰብ ህይወቷ የአውደ አመት ገጠመኞቿ እና የወደፊት እቅዷን በተመለከት ተወያተናል ፡፡



Share